Telegram Group Search
ከክፍልህ ጣሪያ ያልፋል ብለህ
የማታስበው የዱዓ፣ የልመና
ወይም የጥሪህ ድምፅ
ሰባቱ ሰማያትን ያልፋል አብሽር


{ "وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيًّا" }

[ ጌታህም ረሺ አይደለም ]

www.tg-me.com/ISLAM IS UNIVERSITY/com.IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/ISLAM IS UNIVERSITY/com.IslamisUniverstiy_public_group
ፈጣሪ(አሏህ) የለም ብለው የሚያምኑ ሰዎች ጭንቅ ሲላቸው ምን ይሆን የሚያደርጉት? ለማንስ ነው አቤት የሚሉት? ሞክረው/ጥረው አልሳካ ሲላቸው ማንን ይሆን አግዘን የሚሉት?
እኛስ አሏህ አለልን፡፡ አልሐምዱሊሏህ ሙስሊም ያደረግከን ጌታ፡፡ ዱዓ እናደርጋለን፣ ሠላት እንሰግዳለን፣ አዝካር እንላለን መፍትሄም እናገኛለን፡፡

አሏህ መጠጊያችን ነው፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from 
🌤የጧት☀️☀️አዝካር🌤
                     
اصْبَحْنَا وَ أصْبَحَ المُلْكُ لِلَّهِ، وَ الحَمْدُ لِلَّهِ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيْكَ لَهُ، لَهُ المُلْكُ، وَ لَهُ الحَمْدُ، وَ هُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ، رَبِّ أسْألُكَ خَيْرَ مَا في هَذَا اليَوْمِ وَ خَيْرَ مَا بَعْدَهُ، وَ أعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا في هَذَا اليَوْمِ وَ شَرِّ مَا بَعْدَهُ، رَبِّ أعُوذُ بِكَ مِنَ الكَسَلِ، وَ سُوءِ الكِبَرِ، رَبِّ أعُوذُ بِكَ مِنْ عَذَابٍ في النَّارِ وَ عَذَابٍ في القَبْرِ.

ማለዳ ላይ ለመድረስ ነቅተናል፡፡ በዚህ ሰዓት ሉዓላልነት የዓላማት ጌታ የሆነው አላህ ነው፡፡ ምስጋና ከአላህ ነው፡፡ ከአላህ ውጭ ሌላ\አምላክ የለም፡፡ አንድ ነው፡፡ አገር የለውም፡፡ ሉዓላዊነት የርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም የርሱ ብቻ ነው፡፡ ጌታዬ ሆይ የዚህን\ቅና የቀጠዩን የሌሊቱን መልካም ነገር እጠይቅሃለሁ፡፡ ከዚህ ቀንና ከቀጣዩ ከሌሊቱ ክፉ ነገር በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ጌታዬ\ሆይ ከእሳት ቅጣት ከቀብር ውስጥ ቅጣትም በአንተ እጠበቃለሁ፡፡
ازكار الصباح
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Audio
قَالُوا إِنَّا كُنَّا قَبْلُ فِي أَهْلِنَا مُشْفِقِينَ فَمَنَّ اللَّهُ عَلَيْنَا وَوَقَانَا عَذَابَ السَّمُومِ

[አጥ-ጡር 26-27]
“እኛ ፊት በቤተሰቦቻችን ውስጥ (ከቅጣት) ፈሪዎች ነበርን” ይላሉ። “አላህም በእኛ ላይ ለገሰ። የመርዛም እሳት ቅጣትንም ጠበቀን።” 


««የአላህ ፍርሃት ልብ ውስጥ ከሰፈረ፣የስሜታዊ ዝንባሌዎችንና የቁሳዊ ፍላጎቶችን ሰፈሮች አቃጥሎ ዱንያን ከልብ ያስወጣል። አላህም በዕለተ-ቂያማ የአርሽ ጥላ እንጂ ሌላ ጥላ በሌለበት ወቅት በዚሁ ጥላ ከሚጠለሉት ሰዎች መካከል ያደርገዋል።

ورجل دعته امرأة ذات منصب وجمال فقال: إني أخاف الله

“አንድ ሰው አንዲት በዘሯ የተከበረችና ውበት ያላት ሴት ለብልግና ስትጠራው እኔ አላህን እፈራለሁ ያለው ነው”

««አላህ ለሚጠነቀቀው ሰው መሃሪ ነው፣ በወንጀል ላይ ዘውትሯ አላህ ፊት መቆምን ለፈራና ለተፀፀተ ምህረቱ ብዙ ነው።
የቀለበት አደራረግ

ሴት ልጅ የወርቅም ይሁን የብር ቀለበት በፈለገችው ጣት ላይ ማድረግ ትችላለች። ነገር ግን ቤት ውስጥም ይሁን ከቤት ውጪ ስትሆን ጌጧን ባዕድ/አጅነቢይ ወንድ እንዳያይ ጌጡን መሸፈን ግዴታ ይሆንባታል። ይህም የቁርኣን ህግና ትእዛዝ ነው።

ወንድ ልጅ ግን የወርቅ ቀለብት ማድረግ አይችልም። ከወርቅና ከብረት ውጪ ካሉ ነገሮች የተሰራ (የብርም ይሁን ሌላ) ቀለበት ሲያደርግ በመጨረሻው ትንሹ ወይም ከሱ ቀጥሎ ባለው ጣት እንጂ በመሃለኛው ረጅሙ ጣት፣ ከሱ ቀጥሎ ባለው ሌባ (አመልካች) ጣትና አውራ ጣት ላይ ለወንድ ልጅ ቀለበት ማድረግ አይቻልም።
በተለይ በመሃለኛው ረጅሙ ጣትና ቀጥሎ ባለው አመልካች ጣት ላይ ቀለበት ማድረግን ነቢዩ صلى الله عليه وسلم
በግልጽ ከልክለዋል።
ከመሆኑም ጋር ብዙ ወንዶች በነዚህ ጣቶች ቀለበት ሲያደርጉ ይታያል።
ዲናችንን እንወቅ! እውቀት ብርሃን ነው፤ አላዋቂነት ጨለማ ነው።

ኡስታዝ አሕመድ ኣደም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዩሱፍ ጠፋ አባቱም የ ዓይን ብርሃኑን አጣ..!!
●ጉዳዮቼን ሁሉ ወደ አላህ አስጠጋለሁ ብሎ በተናገረ ሰዓት ግን  ....ዩሱፍንም አገኘ የ ዓይን ብርሃኑም ተመለሰለት!!
.
.
ጉዳያቹን ሁሉ ወደ አላህ አስጠጉት ከዛማ ልክ እንደ ነቢዩላህ ያዕቁብ  መፍትሔን ታገኛላችሁ
🐝 የማር ነጋዴ አንድ የቆምጣጤ ነጋዴን እንዲህ ብሎ ይጠይቀዋል:
ሰዎቹ ምን ሆነው ነው ካንተ እየገዙ እኔን ትተው የሚያልፉት ብሎ ጠየቀው !!
ነጋዴው እንዲህ አለው አንተ የምትሸጠው ማር ነው ግን ምላስህን እንደቆምጣጤ ነው ምትጠቀመው እኔ የምሸጠው ቆምጣጤ ነው ግን ምላሴን ምጠቀመው እንደ ማር ነው ብሎ መለሰለት!!

መልእክት : ሰዎችን በስነምግባርህ ተቆጣጠራቸው ¡¡
http://www.tg-me.com/ISLAM IS UNIVERSITY/com.IslamisUniverstiy_public_group
http://www.tg-me.com/ISLAM IS UNIVERSITY/com.IslamisUniverstiy_public_group
በአንድ እጁ ቁራጭ ብስኩት በሌላኛው እጁ ደግሞ የሽንት መሽኛ ከረጢጥ ተሸክሞ ኩላሊቱን እስኪታጠብ ተራውን እየጠበቀ በሆስፒታሉ ውስጥ ይንከራተታል።
በሆስፒታሎች ውስጥ ሌላ ዓለም አለ ስለ ዱኒያ ፍቅር, ምኞት, ገንዘብ አያወሩም ጤናን ብቻ ይጠይቃሉ.
አምላኬ ሆይ ታካሚን ሁሉ ፈውስ ያረብ!!
.
.
ስላለህ ነገር ሁሌም አመስጋኝ ሁን
ኢላሂ ምህረትህን ጌታዬ በሽታ ላደከመው ሁሉ🙏

http://www.tg-me.com/ISLAM IS UNIVERSITY/com.IslamisUniverstiy_public_group
http://www.tg-me.com/ISLAM IS UNIVERSITY/com.IslamisUniverstiy_public_group
ፈጣሪን አግኝቼ የመጠየቅ ዕድል ቢኖረኝ

አልበርት አይንስታይን እንዲህ ይላል:: ፈጣሪን አግኝቼ ጥያቄ መጠየቅ ብችል  ዓለምን(Universe) ለምን እንደፈጠረ እጠይቀው ነበር፡፡ ዓለምን ለምን እንደፈጠረ ካወቅኩ በኋላ እኔ ለምን እንደተፈጠርኩ አውቅ ነበር ይላል፡፡

እስልምና ውስጥ ግን እርሱ ለጠየቃቸው  ጥያቄዎች መልስ አለ፡፡

ጥያቄ 1. የሰው ልጅ ለምን ተፈጠረ?
መልስ፡- وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
[ ሱረቱ አል-ዛሪያት - 56 ]
ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡


ጥያቄ 2. ለምን ይህንን አለም ፈጠረ?
መልስ፡
✔️ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ {الذاريات:56
✔️ هُوَ الَّذِي خَلَقَ لَكُم مَّا فِي الأَرْضِ جَمِيعاً  {البقرة:29
✔️ وَسَخَّرَ لَكُم مَّا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا مِّنْهُ  {الجاثية:13
✔️  الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ الأَرْضَ فِرَاشاً وَالسَّمَاء بِنَاء وَأَنزَلَ مِنَ السَّمَاء مَاء فَأَخْرَجَ بِهِ مِنَ الثَّمَرَاتِ رِزْقاً لَّكُمْ  {البقرة:22
✔️ وَهُوَ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ النُّجُومَ لِتَهْتَدُواْ بِهَا  {الأنعام:97
"" በአጭሩ…አላህ(ሱ.ወ) በሰማይም በምድርም እንዲሁም በውስጡ ያሉ ነገሮች በሙሉ  መጠቀሚያ(መገልገያ) እንዲሆኑላችሁ ነው የፈጠርኳቸው ይለናል፡፡ ""

الحمد لله على نعمة الاسلام

✍️ዐምማር ዐሊ
«ከጥቂት ጭፍራ በአላህ ፈቃድ ብዙን ጭፍራ ያሸነፈች ብዙ ናት፤ አላህ ከታጋሾች ጋር ነው» አሉ፡፡ »
[አልበቀራህ 249 ]

አላህ እውነትን ተናገረ!
 
1979 በሀረም ላይ ምን ተፈጥረ?

በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ግለሰብ ጁሀይማን አልዑተይቢ እና ተከታዮቹ በሱዑዲ እስር ቤት ውስጥ የተነሱት ፎቶ ነው።

ጁሁይማን በቀደምት ዘመኑ የሳዑዲ ዓረቢያ ፖሊስን በመቀላቀል የ«ሳጅን»ነት ደረጃ መድረስ የቻለ ፤ በመዲና ዩኒቨርስቲ ተቀላቅሎም ዲን የቀማመሰ ወጣት እንደሆነ ይነገርለታል። ያኔ የመዲና ዩኒቨርስቲ ውስጥ እጅጉን ተፅኖ እንዳሳደሩበት ከሚነገርላቸው መምህራኖቹ መካከል አንዱ «ሙሐመድ ብን ዓብደላህ አልቀህጧኒ» የተባሉ ሸይኽ ነበሩ። ታሪኩ የሚጀምረውም እዚው ጋር ነው።

ሙሐመድ አልቀህጧኒ ራሳቸውን ልክ እንደ «መህዲ» አድርገው ያምኑ ነበር። የስማቸው መመሳሰል ፣ የአባታቸው ስም አብደላህ መሆን ቁርጥ መህዲን መምሰሉ አሞኝቷቸዋል። በዚህ የጦዘ ምልከታ ውስጥ የፖሊስ አዛዥ ከተማሪያቸው መካከል አንዱ ሲሆን ልባቸው ካዕባን ለመቆጣጠር ሸፈተ። አስበውም አልቀሩም ፤ ጁሀይማንን አሳምነው እና ሴት ልጃቸውን ድረውለት ተከታያቸው አደረጉት።

በአውሮጳዎች መቁጠሪያ ኖቬምበር 20 ቀን 1979 አመት ላይ ጁሀይማን በስውር ያደራጃቸውን ተከታዮች አስከትሎ በጠዋቱ ወደ ሀረም ዘለቀ። ተከታዮቹ በትከሻቸው ላይ አንዳች የጀናዛ ቃሬዛ የመሰለ ነገር ተሸክመዋል።

ድንገት ፈጅር ተሰግዶ እንዳለቀ ግን ጁሀይማን እና ተከታዮቹ የጀናዛ ቃሬዛውን ገለጥ አድርገው የተራቀቁ የጦር መሳሪያዎችን እየመዘዙ ሰጋጁን ያስጨንቁት ያዙ። «መህዲ መቷልና ቃል ግቡለት» ፣ «ኸሊፋቹ ተገልጧልና ተከተሉት» እያሉ አዋከቡት።

አስቀድሞ ትእዛዝ የተቀበሉት ተከታዮቹም በመስጊዱ ሚናራዎች ላይ ስናይፐራቸውን ጠምደው የሀረም ጠባቂ ፖሊሶችን አናት እያፈረጡ ደመ ከልብ አደረጓቸው። ሀረም ተጨነቀች። የመንግስት አካላት ሳይቀሩ መፍትሄው ግራ ሆነባቸው።

©ኢትዮ ሙስሊምስ

ክፍል 2 ይቀጥላል
1979 በሀረም ላይ ምን ተፈጠረ?
ክፍል 2

ሙሐመድ አልቃሕጣኒ እና ጁሀይማን አልዑተይቢ የሀረምን ማይኮሮፎን እያበሩ ውስጥ ላሉት የሐረም እንግዶች እና መስጂዱን ከበው ለተቀመጡት የፖሊስ አዛዦች የማስፈራሪያ እና መህዲን ተቀበሉ መልእክት ያስተላልፋሉ። በከባቢው ላይ የተሰማሩት ፖሊሶች ሀረምን መግባት እንችል እንደው ብለው ወደ በሩ ጠጋ ባሉ ቁጥር ሚናራዎች ላይ የተጠመዱት ስናይፐሮች ስራቸውን ይሰራሉ።

በቦታው ያሉት የፖሊስ ሀይላት ጉዳዩ በቀላል እንደማትፈታ ስለገባቸው የሀገሬው ሰራዊት ስራውን እንዲከውን ወደ መከላከያ ሚኒስትሩ ስልካቸውን አንቃጨሉና የሱዑዲያ ወታደሮች በተራቸው ሀረምን ከበው እገታውን ለመስበር ያላቸውን ሀይል ሁሉ አፈሰሱ። ሁኔታው ግን ምንም አልተለወጠም።

በመሆኑም አጋቾቹን ለማዳከም የሀረም ውሀ አገልግሎት እና የመብራት ስርጭት ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ ተደረገ። ግን የተጠበቀው ውጤት ተቀልብሶ ከአጋቾቹ ይልቅ የሐረም እንግዶች በጥማት እና ረሐብ በየቦታው መወዳደቅ ጀመሩ። ንጉስ ዃሊድ ቢጨንቀው ሽማግሌ አስልኮ ከበዛ ንትርክ በኋላ በመጅጂዱ ክልል ያሉ ህፃናት እና ሴቶች ያለምንም መታኮስ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ተፈቀደላቸው። እርግጥ እነ ዑተይቢ ስንቅ እያለቃቸው ስለነበር ከዚህ የተለየ የመደራደሪያ መንገድ አልነበራቸውም።

ሀረም እንዲህ በእገታ በተሟሟቀችበት ወቅት አሜሪካ እና ኢራን የጉዳዩ ጠንሳሽ አንቺ ነሽ! አንቺ ነሽ! እየተባባሉ አጋጣሚውን ለፖለቲካ ጥቅማቸው መጓተቻ ለማድረግ በየሚዲያው ይንተፋተፋሉ።

እንዳይታኮሱበት ሀረም ፤ ዝም እንዳይሉም መንግስት ግልበጣ ሆኖባቸው የተወዛገቡት ባለስልጣናት ጉዳዩን ወደ ፈታዋ ምክር ቤት መርተው የሀረምን ክብር ለማስጠበቅ ሲባል ወታደራዊ እንቅስቃሴ በውስጡ ማድረግን የሚፈቅድ አዲስ ፈታዋ ተቀብለው በየጋዜጣው እና ሚዲያ ማሰራጨት ጀመሩ።
1979 ሀረም ላይ ምን ተፈጠረ?
ክፍል 3

«ሀይአት ኪባረል ዑለማ» የሰዑዲ ፈታዋ ምክር ቤት በሀረም ከባቢ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዲደረግ የሚፈቅድ ፈታዋ ሲሰጥ እንዲህ ቀላል አልነበረም። ምክኒያቱም ከአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) የተገኙ ትክክለኛ እና ግልፅ ሀዲሶች በሀረም ዙርያ ወታደራዊ እርምጃዎችን ይከለክላሉ።  ስለዚህ ፈታዋቸው ከትችት የነፃም ሆነ የዓለም ዑለማዎችን በ2 ጎራ ከፍሎ ከማነታረክ ሊተርፍ አይችልም።

ዞሮዞሮ ፈታዋው ከተሰጠም በኋላ በትንሽ ሰብአዊ ኪሳራ ሀረምን ከእገታ የማዳኑን ሀላፍትና ማን ይውሰድ የሚለው ለንጉስ ኻሊድ ሌላ ራስ ምታት ሆኖበታል። የሀገሬው ፖሊስ የሞከራቸውም ፤ የሀገሬው ሰራዊት አሳክቼዋለው የሚለው አንድም ፍሬ ነገር ማቅረብ አልቻለም።

ስለዚህ ከውጪ ሀገር ኮማንዶዎች ይህንን   ተግባር አቀላጥፎ የሚጨርስ መረጣ በጠረጴዛ ዙርያ ሲጣል ሲነሳ ከቆየ በኋላ የፈረንሳይ ኮማንዶ ተመረጠ። ኮማንዶው አለኝ የሚለውን ዘመናዊ መሳሪያ አንግቦ የሱዑዲያ ምድር ከተመ። ግን ስራውን ገና ሳይጀምር ከበድ ያለ ፈተና ገጠመው። የሀረም ክልል ውስጥ ሙስሊም ያልሆኑ ሰራዊቶች እንዴት ሊገቡ ይፈቀድላቸዋል? የሚል። ጥያቄው በምን መልኩ እንደተፈታ ብዙ መላምቶች ቢሰነዘሩም የፈረንሳይ ኮማንዲ ቡድን ሀረምን ከእገታ በማስለቀቁ ላይ የአምበሳውን ድርሻ እንደወሰደ የትኛውም ተራኪ የማይክደው እውነታ ነው።

ኮማንዶው ሀረም የገባው ሸሀዳ ይዞ ነው ፤ ኮማንዶው አመራር እና ሎጅስቲክ ላይ ብቻ ነው የተሳተፈው እና ሌሎችም ተብሏል።

ኮማንዶው በሀረም የመሬት ስር መንገድ በመግባት መርዛማ ጪሶችን ወደ ሀረም ክልል አስወነጨፈ። የሀረም እንግዶች በከባድ ሳል እየተጨነቁ የድረሱልን ሰቆቃ ድምፅ ያሰማሉ። በጪሱ ነቦልቧል የተጨነቀው ሀረም በላዩ ላይ የጥይት እሩምታ ታከለበት። ሰላማዊው ክልል የጦር አውድማ ሆነ።
1979 ሀረም ላይ ምን ተፈጠረ?

የመጨረሻ ክፍል

የመስጂደል ሀረም ግቢ እገታ እንደቀልድ 14 ቀናት ጨርሶ 15ኛ ቀኑን ይዟል። በአለም ዙሪያ ያሉ ሙስሊም በዝ ሀገራት ህዝቦችም የሀረምን መታገት በመቃወም በየቦታው የቁጣ ድምፅ ያዘሉ ሰላማዊ ሰልፎችን አጧጡፈውታል።ንጉስ ኻሊድ የመጨረሻ እምነቱን የጣለባቸው የፈረንሳይ ኮማንዶዎች ሙስሊም ናቸው ወይ? የሚለው ንትርክ ሳይቋጭ ወደ መስጂደል ሀረም ዘልቀው ስራቸውን «ሀ» ብለው የጀመሩትም እገታው ከተፈፀመ 15 ቀናት በኋላ ነበር።

ኮማንዶዎቹ በመስጂደል ሀረም የመሬት ለመሬት መንገድ እየተሽሎከሎኩ ገብተው መርዛማውን ጭስ ወደ ሀረም ካስወነጨፉት በኋላ ድንገተኛ እና ያልጠበቁት ጥቃት የደረሰባቸው የዑለይቢ ቡድኖች ባገኙት አቅጣጫ ሁሉ ይተኩሳሉ። ኮማንዶዎቹም ጭንብላቸውን እንዳጠለቁ አጋች ነው ብለው ያሰቡትን በጥይቅት ይቆሉታል። በመካከል ግን የሀረም እንግዶች ከቀኝ እና ግራ በሚተኮሱ ጥይቶች እና ሀረምን ባጠነው መርዛማ ጭስ ህይወታቸው ወደ ቀጣዩ አለም ትከንፋለች።

ከብርቱ ፍልሚያ በኋላ ከዑተይቢ ቡድኖች መካከል አንድ ጉምቱ ሰው በጥይት ተጠብሶ መሬት ላይ ተዘረረ። ብዙም ሳይቀለይ ስትንፋሱ ተቋርጣ ሽቅብ ጥላው ከነፈች። ዑተይቢና ተከታዮቹ ያዩትን ማመን አልቻሉም። እሱን እስከያዝን አለምን እንገዛበታለን ያሉት መህዲያቸው ገና በመጀመሪያው ፍልሚያ ህይወቱን ተነጠቀ። አዎን! የሞተው መህዲ ነው ብለው ያሰቡት ሙሐመድ ብን ዓብደላህ አልቀሕጧኒ ነበር።

ከዚህ ወዲያ ፍልሚያም ሆነ መስዋእትነት ለነዑተይቢ ትርጉም የለውምና ቀስበቀስ መሳሪያቸውን እየጣሉ እጃቸውን ለኮማንዶው እጃቸውን ሰጡ። ፍልሚያውም ከ15 ቀን አስጨናቂ ትግል በኋላ ተጠናቀቀ። አማፂያኑም ከጥቂት የፍርድ ሂደት በኋላ በአደባባይ የሞት ፍርዳቸውን ተቀብለው ወደ ቀጣዩ የአላህ ፍርድ ተሸኙ።
" !عيدكم مبارك "
ዒድ ሙባረክ!
Eid Mubarak!

"تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال"

ከእኛም ከእናንተም አሏህ መልካም ስራዎቻችንን ይቀበለን!

እንኳን ለ1445ኛው ዓ.ሂ የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡

ዒድ ሙባረክ!
2024/06/17 20:18:47
Back to Top
HTML Embed Code: